አዲሱን ቤተክርስትያን ለማሰራት የበኩሎን ይወጡ

”የእግዚአብሔርን ቤት ለመሥራት ይወጡ ዘንድ እግዚአብሔር መንፈሳቸውን ያነሣሣው ሁሉ ተነሡ።” ዕዝ 1፥5

የእግዚአብሔር ቅዱስ ፈቃድ ሆኖ በአይነቱ ለየት ያለውን እና አዲሱን ቤተክርስትያን ተለቅ አድርገን ለመስራት ቆርጠን ከተነሳን ይኸው 10 ወራትን አስቆጥረናል። የቤተክርስትያኑን ግንባታ ለማስጀመር መነሻ ይሆነን ዘንድ በወር 300 ክሩነር ምዕመናን እንዲያዋጡ ፎርም አስሞልተን ነበር። በወር 300 ክሩነር ለማስገባት ቃል በገባችሁት መሰረት ቃላችሁን ሳታጥፉ ያለመሰልቸት እየክፈላችሁ ያላችሁትን ምዕመናን ከልብ እያመሰገንን። ቃል ገብታችሁ ሳትከፍሉ የዘነጋችሁትን ምዕመናን በሐያሉ እግዚአብሔር ስም እንድትከፍሉ ልናሳስባችሁ እንወዳለን።
የመንፈሳዊ አገልግሎት መርሐ ግብር

የስቶክሆልም ደብረሰላም መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ዘወትር ረቡዕና ዓርብ ከምሽቱ 18:00 እስከ 20:00 ሰዓት
1. የሠርክ ጸሎት
2. የትምህርተ ወንጌል
አገልግሎት ለምዕመናን የምትሰጥ መሆኗን በታላቅ መንፈሳዊ ደስታ እየገለጸች፤ የመንፈሳዊ አገልግሎቱ ተሳታፊ እንድንሆን ጥሪዋን ታስተላልፋለች።