ቋንቋ ለማስተማር

በደብረሰላም መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን የሚካሄድ የአማርኛ ትምህርት ለህፃናትና ለጎልማሶች ከመጋቢት አስር(10) 2003 ወይም በአውሮፓውያን አቆጣጠር Mars አስራ ዘጠኝ(19-2011)ዘወትር ቅዳሜ ከሰባት ሰዓት(13፡00)እስከ አስራ አንድ (17፡00)ሰዓት በሮግስቬድ(Rågesved Folkets Hus)ተጀምሮአል። የሚሰጡት የትምህርት አይነቶች፡ የአማርኛ ፊደል ማንበብና መጻፍ፣ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ኃይማኖትን ታሪክና እና እምነት ማስተማር፣ የሃገራችንን ታሪክና ባህል ማሳወቅ። ይህንን እና ሌሎችም እንደ አስፈላጊነቱ እየታየ በቅድመ ተከተል ይቀጥላል። ለለመመዝገብም ሆነ ለማንኛው ጥያቄ ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት እና ቦታ ሊመጡ ይችላሉ። ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 070-9522847 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ።