በታላቅ ድምቀት ተከበሮ ዋለ
የሊቀ መልአኩ የቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል እና 17 ኛው በአውሮፓ የኢትዮጵያ ኦርቶዶስ ተዋሕዶ አብያተ ክርስቲያናት መንፈሳዊ ጉባኤ በእግዚአብሔር ፈቃድ በታላቅ ድምቀት ተከበረ።
ሐምሌ 19 በየዓመቱ የሚከበረው የ ቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል በታላቅ ድምቀት ተከበረ። በክብረ በዓሉ ላይ ብጹዕ አባታችን አቡነ ኤልያስ፣ ሊቃዉንተ ቤተ ክርስትያን አባቶች፣ ሊቀ መዘምር ዲያቆን ቴውድሮስ ዮሴፍ፣ ሊቀ መዘምር ይልማ ሃይሉ፣ ዶክተር ቀሲስ አንዱዓለም የተገኙ ሲሆን ክብረ በዓሉን ለማክበር ከተለያዩ የአውሮፓ አገራት የተሰባሰቡት ምዕመናን ቁጥር እንዲህ ነው ሚባል አልነበረም።
ከ ቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ ክብረ በዓልም በተጨማሪ በጉተንበርግ የመላው አውሮፓ 17 ኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶስ ተዋሕዶ አብያተ ክርስቲያናት መንፈሳዊ ጉባኤ መርሐ ግብር በጥሩ መንፈስ በእግዚአብሔር ፈቃድ በ አማረ እና ምዕመናኑን ሁሉ ባስደሰተ መልኩ ተጠናቆአል።
ሁሉም ነገር የተከናወነልን ታላቅ በሆነው እና ወደር በማይገኝለት በእግዚአብሔር ቅዱስ ፈቃድ ነዉና ክብር እና ምስጋና ለፈጣሪያችን ይሁን። አሜን !
ከጉባዔው የተወሰደ ቪድዮ
የጥቅምት መድኃኔዓለም አመታዊ ክብረ በዓል ታቦተ ህጉ ወጥቶ በታላቅ ድምቀት ተከብሮ ዋለ።
በዓሉን በተመለከተ ለሦስት ቀን ከተካሄደው መንፈሳዊ ጉባዔ የየቀኑን ትምህርት
እና በዓሉ ምን ያህል አስደሳች እንደነበር ለማሳየት በቪድዮ የተወሰዱትን በቅርቡ እናወጣለን።
ከመጀመሪያው ቀን የተወሰደ ቪድዮ