የአስራ አራተኛው መንፈሳዊ ጉባኤ

እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ከሐምሌ 8 2003(ጁላይ 15 2011) ጀምሮ እስከ ሐምሌ 10 2003(ጁላይ 17 2011) ሲካሄድ የቆየው የአስራ አራተኛው ታላቅ መንፈሳዊ ጉባኤ በአስደሳች ሁኔታ ተጠናቀቀ።
በብፁዕ አባታችን አባ ኤልያስ በአውሮፓ፣ በምሥራቅና ደብብ አፍሪቃ የኢትዮጰያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ ቡራኬ ተሰጥቶ ከተጀመረበት መጀመሪያ ቀን ጀምሮ በተለያዩ የእግዚአብሔር ፀጋው በበዛላቸው መምህራን፣ ዘማሪያን እና መዘምራን ግሩም የሆነ መንፈሳዊ ትምህርት እና ዝማሬ በማቅረብ የጉባኤውን ታዳሚ ልዩ በሆነ መንፈሳዊ ስሜት ሲያወያይ ውልዋል።
ይህ በማናቸውም መልክ ልዩ የሆነ ከተለያየ ሃገር በመጡ ካህናት አባቶች እና ምዕመናን የተሳተፉበት ጉባኤ ምን ይመስል እንደነበር ለማየት ከታች ያስቀመጥነውን ቪድዮዎች ይመልከቱ።

ከአውሮፓ አስራ አራተኛው መንፈሳዊ ጉባኤ የተወሰዱ የተለያዩ ቪድዮዎች


የብፁዕ አባታችን አባታዊ ምክር

ከአውሮፓ ከተለያዩ ሃገሮች የመጡ መዘምራን በአንድ ላይ የምስጋና መዝሙር ሲያቀርቡ